Tenders

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር ድ/ዳ/ዩ/ግ/ጨ/06 / 2015

የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ለ2015 ዓ.ም Supply and Implementation of Advanced Enterprise Antivirus Software and HCI Solution አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ህጋዊና ብቃት ያላቸውን የሀገር ውስጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

በዚህም መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

1-       የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 9 ከተጠቀሱት አድራሻዎች ለእያንዳዳቸው የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በዩኒቨርስቲው አካውንት ቁጥር 606C21002728 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስገብታቹ ደረሰኝ  በማምጣት የጨረታ ሰነዱን  መውሰድ ይችላሉ፤

2-       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሰኔ 26/10/2015 ዓ.ም ከጥዋቱ 400 ሰዓት ድረስ በተ.ቁ 9 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

3-       የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት እና ቦታ ከጠዋቱ 415 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

4-       ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው አካተው መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው፤

4.1.      በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውና ለዘመኑ ስለመታደሱ የተረጋገጠ፤

4.2.      ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ግብርና ታክስ ለመክፈላቸው ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣታቸው ማረጋገጫ፤

4.3.   በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችልማስረጃ ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ተጫራች ድርጅቶች የተጠቀሰውን ማስረጃ ሲያቀርቡ ማስረጃው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የተሰጠ ማስረጃ ብቻ መሆን እንዳለበትና በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተሰጠ ማስረጃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን፡፡

4.4.      የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤

4.5.      ተጫራቾች ዩኒቨርሲቲው ባወጣው የጨረታ ሰነድ ውስጥ በተጫራቾች የሚሞሉ ቅጾችን በትክክል ሞልተው በመፈረም እና ማህተም በማድረግ መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.6.      ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከዚህ በታች በተገለፀው ሰንጠረዥ መሰረት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

4.7.      ከዚህም በተጨማሪ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋስትና የጨረታ ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት ቀን በኋላ ላሉት 28 ቀናት ዋስትናውን ሕጋዊነት የሚያረጋግጥ መሆን ይኖርበታል፡፡

ተ.ቁየእቃዎች መግለጫጨረታ ማስከበሪያ መጠን
1Supply and Implementation of Advanced Enterprise Antivirus Software and HCI Solution100,000.00

5-       ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የስራ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች አቅርቦቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6-       ዩኒቨርሲቲው የተጫራቾችን ብቃት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መስፈርቶች፣ የጨረታ መመሪያዎችና ሌሎችም ተዛማጅነት ያላቸውን መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ያካተተ ስለሆነ በሁሉም ተሳታፊ ተጫራቾ እንዲተገበሩ ያሳስባል፤

7-       ተጫራቾች ስለ ማጭበርበር እና ሙስና ላለመፈፀም ማረጋገጫ በመስጠት ግዴታ የሚገባበትን ቅጽ በመፈረም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

8-       ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፤

9-       ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤

ድሬዳዋ ዩኒርቨሲቲ ቢሮ ቁጥር – 4

ስልክ ቁጥር 0251 12 78 63

ፋክስ ቁጥር 0251 12 79 71/77

ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1362

የጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ ልዩ ልዩ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ የአስፓልት በርሜሎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ቁጥር PPS/NVP-3FBI/09/09/2015

የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጂማ ዲስትሪክት በ 3 ቦታዎች የሚገኙ ያገለገሉ ጎማዎች፣ የአስፓልት በርሜሎችንና ባትሪዎችን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በአዲስ አበባ በሚገኘው የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 007 በመምጣት የንብረቶቹን መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣

3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣

4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ መንግሥት ግዥ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 007 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርቱ ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡

6. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

7. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣

8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

9.  አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡

10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል አስተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዝብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡

11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣

12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-122 37-08/ ወይም 011-154-04-25 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣

13. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

Translate »
Scroll to Top
Apex Business Consultancy